የደቡብ እና የምስራቅ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ እና የመከላከያ ሚኒስትሮች በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጉዳይ የማያደርጉት ስብሰባ ዛሬ እና ነገ በዚምባብዌ አንደሚካሄድ ተገለጸ

የደቡብ እና የምስራቅ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ እና የመከላከያ ሚኒስትሮች በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጉዳይ የማያደርጉት ስብሰባ ዛሬ እና ነገ በዚምባብዌ አንደሚካሄድ ተገለጸ የስብሰባው አላማ በአንጎላ ፕሬዝዳንት ጃዎ ሎሬንሶ አደራዳሪነት በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና በኤም 23 አማፂያን መካከል ማክሰኞ እለት በሉዋንዳ ለሚደረገው ውይይት መዘጋጀት እንደሆነ የኮንጎ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ተሳታፊዎች በደቡብ አፍሪካ ልማት ማህበረሰብ (ሳድክ) ሀገራት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሞች እና የጦር አዛዦች በሚያቀርቡት ሪፖርት ላይ ይወያያሉ። ሪፖርቱ በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በኤም23 መካከል ያለውን ግጭት ማስቆም፣ ሕዝቡ እርዳታ እንዲያገኝ ማድረግ እና ለቀጣይ የፖለቲካ ምክክር ፍኖተ ካርታ መፍጠር ላይ ያተኩራል ተብሏል። የሀራሬው ስብሰባ የሳድክ እና የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ መሪዎች በታንዛኒያ ዳሬሰላም ባወጡት የጋራ የመሪዎች ውሳኔ መሠረት የተዘጋጀ ነው።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik