ደቡብ አፍሪካ አምባሳደሯ ከዋሽንግተን ቢባረሩም ከአሜሪካ ጋር ግንኙነቴን እቀጥላለሁ አለች

ደቡብ አፍሪካ አምባሳደሯ ከዋሽንግተን ቢባረሩም ከአሜሪካ ጋር ግንኙነቴን እቀጥላለሁ አለች "ፕሬዝዳንቱ በዩናይትድ ስቴትስ የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር ኢብራሂም ራሱልን የሚያስቆጭ የመባረር ውሳኔ ሰምተዋል" ያለው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት "ሁሉም የሚመለከታቸው እና በውሳኔው የተነኩ ባለድርሻ አካላት ጉዳዩን በተመለከተ የተለመደውን ዲፕሎማሲያዊ አግባብ እንዲጠብቁ ያሳስባል" ሲል ባወጣው መግለጫ አስገንዝቧል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በዋሽንግተን የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር ኢብራሂም ራሱል “አሜሪካን እና ፕሬዝዳንቷን የሚጠሉ፤ ዘረኝነትን የሚያበረታቱ ናቸው በማለት ከዩናይትድ ስቴትስ እንዲወጡ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።ራሱል በፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በዩናይትድ ስቴትስ የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር ሆነው በድጋሚ የተሾሙት በህዳር ወር ነበር። የሹመት ደብዳቤያቸውን በጥር ወር ለቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ያቀረቡት ራሱል፤ እ.አ.አ ከ2003 እስከ 2008 ድረስ በተመሳሳይ የኃላፊነት ቦታ አገልግለዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik