የኢትዮጵያ እና ሩሲያ ባህር ኃይሎች በትብብር መሥራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩበሩሲያ ባህር ኃይል ምክትል አዛዥ አድሚራል ቭላዲሚር ቮሮቢቭ የሚመራ የልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ተቋማትን፣ ጠቅላይ መምሪያውን እና ቢሾፍቱ የሚገኘውን ማሰልጠኛ ማዕከል ጉብኝቷል።በተጨማሪም ሩሲያ ከኢትዮጵያ ባህር ኃይል ጋር በጋራ ልትሠራባቸው እና ትብብር ልታደርግባቸው በምትችላቸው ጉዳዮች ዙርያ ውይይት ማድረጋቸውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አስታውቋል። የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ምክትል አዛዥ ኮሞዶር ጀማል ቱፊሳ ትብብሩ በስልጠና እና አቅም ግንባታ ዙሪያ እንደሚያተኩርና በዓለም አቀፍ ውሃ ላይ የኢትዮጵያን ጥቅም ለማስጠበቅ ዝግጁነቷን የበለጠ ለማጠናከር የሚያግዝ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia