ኢትዮጵያ በ2026 ሶስተኛውን የምድር ምልከታ ሳተላይት ከቻይና ጋር በመተባበር ለማምጠቅ ማቀዷን አስታወቀችአዲሱ ሳተላይት ከቀደምቶቹ አንፃር የተሻሻለ የምስል ጥራት ይኖረዋል መባሉን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ሳተላይቱ የአካባቢ ቁጥጥርን፣ የአደጋ መከላከልን እና የግብርና ዝግጅትን ይደግፋል ተብሏል። የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት የሳተላይት ክትትል ዳይሬክተር ተስፋዬ ፉፋ ሳተላይቱን ለማምጠቅ ቅድመ ዝግጅት ከወዲሁ መጀመሩን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ የመጀመርያውን ሳተላይት ETRSS-01 እ.አ.አ 2019 ያመጠቀች ሲሆን በ2020 ሁለተኛ ሳተላይት አስከትላለች።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia