ደቡብ ሱዳን ወደ የእርስ በእርስ ጦርነት አልተመለሰችም ሲሉ የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣን አስተባበሉስፑትኒክ ያነጋገራቸው የክልሎች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ዴንግ ዴንግ አኮን፤ የወቅቱ የደቡብ ሱዳን ውጥረት ከጸጥታ አደረጃጀት እና የተለያዩ ወታደራዊ ኃይሎችን ወደ ብሄራዊ ጦሩ ከማዋሃድ ጋር በተያያዘ እንደተፈጠረ ተናግረዋል፡፡ፕሬዝዳንት ኪር እና ምክትል ፕሬዝዳንት ማቻር አሁንም በስልጣን ላይ መሆናቸውን የገለፁት ባለስልጣኑ፤ አለመግባባቱን ለመፍታት ድርድር እየተካሄደ እንደሆነ አስታውቀዋል።ምክትል አፈ-ጉባኤው ማቻር በቁም እስር ላይ ናቸው እንዲሁም ከኋየት አርሚ ሚሊሻ ጋር ግንኙነት አላቸው የሚሉ ክሶችን ውድቅ አድርገው፤ የአፍሪካ አሸማጋዮች እና ዓለም አቀፍ አጋሮች ጉዳዩን ለመፍታት ጥረታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia