ኡጋንዳ የደቡብ ሱዳን መዲናን ለመጠበቅ ወታደሮቿን ወደ ጁባ እንደላከች የሀገሪቱ መከላከያ ኃይል አዛዥ አስታወቁ 🪖 የኡጋንዳ ሕዝባዊ መከላከያ ኃይል (ዩፒዴፍ) ልዩ ኮማንዶ ለደቡብ ሱዳን ሕዝባዊ መከላከያ ኃይል ድጋፍ ለመስጠት ከሁለት ቀናት በፊት ጁባ መግባቱን ጄኔራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ በኤክስ ገፃቸው ይፋ አድርገዋል። "የደቡብ ሱዳንን አጠቃላይ ግዛት እንደራሳችን እንጠብቃለን። እኛ ዩፒዲኤፍ ለደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ብቻ ነው እውቅና የምንሰጠው...በእርሳቸው ላይ የሚቃጣ ማንኛውም እርምጃ በኡጋንዳ ላይ እንደታወጀ ጦርነት ይቆጠራል! ያን ወንጀል የፈፀሙ መዘዙን ይቀምሳሉ" ሲሉ ጄኔራሉ አስጠንቅቀዋል። ካይኔሩጋባ በኤክስ ገፃቸው ላይ የለጠፉት ተንቀሳቃሽ ምስል የኡጋንዳ ልዩ ኃይል ኮማንዶ በደቡብ ሱዳን ሲያርፍ ያሳያል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia