ኢትዮጵያ የሰው አልባ አውሮፕላን ማምረቻ ፋብሪካ ከፈተች ስካይዊን ኤርኖቲክስ ኢንዱስትሪ የድሮን ማምረቻ ፋብሪካ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ትናንት ተከፍቷል። ፋብሪካው ብዙ ዓይነት ችሎታ ያላቸው ድሮኖችን በሀገር ውስጥ ባለሞያዎች ዲዛይን አድርጎ የማምረት አቅም እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። አክለውም ኢትዮጵያ ድሮን አምርቶ ከመጠቀም ባሻገር ለውጭ ገበያ ማቅረብ የሚያስችል አቅም መገንባቷን ገልፀዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia