ኢትዮጵያ ሴት አመራሮችን ለማብቃት ተግታ እየሠራች ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ተናገሩ

ኢትዮጵያ ሴት አመራሮችን ለማብቃት ተግታ እየሠራች ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ተናገሩ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ በተዘጋጀ ፕሮግራም ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ሴቶችን በተለያዩ ማሕበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ዘርፎች ለማብቃት ያለሙ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን፣ ፕሮቶኮሎችን እና ቃልኪዳኖችን በማዋሃድ እና ተግባር ላይ በማዋል ረገድ ኢትዮጵያ በአርአያ የምትጠቀስ ሀገር መሆኗን ተናግረዋል።"ሴቶች በሕግ አውጭው፣ አስፈፃሚው እና የፍትህ አካላት ውስጥ ከፍተኛ ቦታ እንዲይዙ መደረጉ ሀገሪቱ አካታች ለመሆን ቁርጠኛ እንደሆነች ያሳያል። ለምሳሌ 41 በመቶ የሚሆነውን የፓርላማ መቀመጫ የያዙት እንዲሁም በተለያየ ግዜ የሚቀያየር ቢሆንም 50 በመቶ የካቢኔ አባላት ሴቶች ናቸው። ይኼም ሴቶች በሀገሪቱ ወሳኝ የፖለቲካ ቦታዎች ውስጥ ቁልፍ ሚና እንዲጫወቱ በማስቻል ረገድ ጉልህ መሻሻሎች እንዳሉ የሚያሳይ ነው" ሲሉ አብራርተዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሴቶች በዲፕሎማሲው ዘርፍ ተሳታፎ እንዲኖራቸው ማበረታታቱን እና ለስኬታማ ድርድር የሚያስፈልጓቸውን መሠረታዊ ችሎታዎች እና እውቀቶች በማቅረብ ማዘጋጀቱን ይቀጥላል ማለታቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ነው የዘገበው። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik