የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ የአዲስ አበባን "አስደናቂ" ለውጥ አደነቁ ፕሬዝዳንቱ ከጆሃንስበርግ ከተማ ምክር ቤት ተወካዮች ጋር ባደሩጉት ውይይት የከተማዋን ለውጥ በማሳያነት አንስተዋል። በቅርቡ አዲስ አበባን ጎብኝቻለው ያሉት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት፤ ከተማዋ ውብና ፅዱ እንደሆነች እንዲሁም ኢንቨስትመንት እና ንግድ እንደተሟሟቀባት አይቻለሁ ብለዋል። "አዲስ አበባ ውብ ከተማ ሆናለች። ዛሬ በአዲስ አበባ ስትንቀሳቀሱ የደመቁ ጎዳናዎች፣ ንፁህ መንገዶችና እያደገ የመጣ የንግድ እንቅስቃሴ" ታያላችሁ ሲሉ ተናግረዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia