ኮትዲቯር እና ጋና የሳህል ሀገራት ጥምረት አባላት ወደ ኢኮዋስ እንዲመለሱ ጥሪ አቀረቡ

ኮትዲቯር እና ጋና የሳህል ሀገራት ጥምረት አባላት ወደ ኢኮዋስ እንዲመለሱ ጥሪ አቀረቡ ከጋና አቻቸው ጆን ድራማኒ ማሃማ ጋር የተገናኙት የኮትዲቯር ፕሬዝዳንት አላሳን ኦውታራ፤ የኮንፌዴሬሽኑ አባላት ለጸጥታ እና ሰብዓዊ ፍላጎቶቻቸው በሚያገኙት እርዳታ ተጠቃሚ ይሆናሉ ብለዋል። ማሃማ "ከሚከፋፍሉን ጉዳዮች ይልቅ አንድ የሚያደርጉን ይበልጣሉ" ሲሉ ተናግረዋል። አክለውም የሶስት ሀገራት ቡድን ውስጥ ከመሆን በ15 ሀገራት ቡድን ውስጥ መሆን የተሻለ ነው ብለዋል። "ሽብርተኝነትን እንዲዋጉ ልንረዳቸው ተዘጋጅተናል። ምክንያቱም የጎረቤትህ ቤት ሲቃጠል ወደ አንተ ግቢ ከመስፋፋቱ በፊት እሳቱን እንዲያጠፋ መርዳት እለብህ" ሲሉ የጋናው ፕሬዝዳንት ተናግረዋል። ኦውታራ የጋናው መሪ የሳህል ሀገራት ጥምረት (ኤኢኤስ) አባላት በምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማሕበረሰብ (ኢኮዋስ) ውስጥ እንዲቆዩ ያሳምናሉ ብለው እንደሚያምኑ ጠቁመዋል። የኤኢኤስ ሀገራት ኢኮዋስን በይፋ የለቀቁት ጥር 21፣ 2017 ዓ.ም ነበር። ሆኖም ውሳኔያቸውን እንዲያጤኑ ተጨማሪ ስድስት ወር ቢሰጣቸውም ሀገራቱ ሃሳቡን ውድቅ አድርገዋል። የቡርኪናፋሶ፣ ኒጀር እና ማሊ መሪዎች ግን ውሳኔያቸው እንደማይቀለበስ አስረግጠዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik