ከ658 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀሚኒስቴሩ ለ2017-18 ዓ.ም የምርት ዘመን ግብዓት የሚሆን ከ700 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ የአፈር ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ መድረሱን አስታውቋል፡፡ለምርት ዘመኑ ከተያዘው የ2.4 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ግዥ ውስጥ እስከ የካቲት 23 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ 700 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ የአፈር ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ መድረሱ ተጠቁሟል፡፡ጅቡቲ ወደብ ከደረሰው የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ 658 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ የሚሆነው ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱን የሚኒስቴሩ መረጃው ያመላክታል፡፡ወደ ሀገር ውስጥ ከተጓጓዘው ማዳበሪያ ውስጥ 418 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ዳፕ ሲሆን 239 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ የሚሆንው ደግሞ ዩሪያ የተሰኘው የአፈር ማዳበሪያ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር በማህበራዊ ትሥሥር ገፁ አስታውቋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia