ጄፍሪ ሳክስ ስለ ኔቶ መስፋፋት እና የዩክሬን ግጭት መሠረታዊ እውነታዎችን በድጋሚ አብራርተዋል ታዋቂው አሜሪካዊ የኢኮኖሚ ባለሙያ ጄፍሪ ሳክስ፤ በዩክሬን ግጭት ዙርያ በስፋት ከሚንፀባረቀው አመለካከት በተቃራኒ የሩሲያ ዋና ግብ አሜሪካ መሩ ኔቶ ወደ ድንበሯ እንዳይጠጋ መከላከል ነው ሲሉ በድጋሚ ሞግተዋል። እ.አ.አ 1991 የሶቭየት ህብረት ከፈራረሰ በኋላ ኔቶ ወደ ምስራቅ እንደማይስፋፋ የጋራ መግባባት እንደነበር አስታውሰዋል። ሆኖም አሜሪካ ይህንን ስምምነት በማፍረስ በ1999 ኔቶን ማስፋፋት እንደጀመረችና በ2004 ይበልጥ እየገፋ መጥቶ፤ በ2008 ዩክሬን እና ጆርጂያ ላይ ማነጣጠሩ በቀጥታ ሩሲያን የቆሰቆሰ እርምጃ እንደሆነ ጠቁመዋል። "ዩክሬን ለመስማማት ጫፍ ደርሳ ትታዋለች። ለምን? ምክንያቱ የአሜሪካ ምክር ነው። ሃሳቡም ዩክሬን፣ ሮማንያ፣ ቡልጋሪያ፣ ቱርክ እና ጆርጂያን ተጠቅሞ ጥቁር ባህርን በመዝጋት ሩሲያን መተንፈሻ ማሳጣት ነው። ከዛም ከምታስቡት በላይ ክፉ፣ የማይታመኑ እና ሙሰኛ የሆኑት የአሜሪካ ሴናተሮች 'አንድም አሜሪካ ስላልሞተ ይህ የገንዘባችን አስደናቂ ውጤት ነው' እንዲሉ ነው። ግልፅ የውክልና ጦርነት ነው” ሲሉ ሳክስ ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia