የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ የዩክሬንን ግጭት በማባባስ የምዕራባውያን መሪዎችን ወቀሱ ሰርጌ ላቭሮቭ ከክራስናያ ዝቬዝዳ ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ፤ የዴንማርክ ጠቅላይ ሚኒስትር ሜቴ ፍሬድሪክሰን 'አሁን ለዩክሬን ከጦርነት ይልቅ ሰላም አስከፊ ሊሆን ይችላል' በማለት ያደረጉትን ንግግር በማሳያነት አንስተዋል፡፡ የሩሲያው ከፍተኛ ዲፕሎማት የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር እና የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ ተጽእኖ ለመፍጠር ጥረት እያደረጉ እንደሆነና ግጭቱን በፍጥነት ከመፍታት ይልቅ ለማራዘም ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia