የኢትዮጵያ አትሌቶች በቶኪዮ ማራቶን በድል አሸበረቁ በዓለም የአትሌቲክስ መድረክ የፕላቲኒየም ደረጃ በተሰጠዉ የቶኪዮ ማራቶን በሁለቱም ፆታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል እንደቀናቸው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌድሬሽን አስታውቋል። በሴቶች የማራቶን ውድድር አትሌት ሱቱሜ አሰፋ 2 ሰዓት ከ16 ደቂቃ ከ31 ሰከንድ በመግባት በአንደኝነት ስታጠናቅቅ፤ በወንዶች ማራቶን አትሌት ታደሰ ታከለ 2 ሰዓት ከ03 ደቂቃ ከ23 ሰከንድ በመግባት አሸንፏል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia