የኢትዮ-ሶማሊያ ግንኙነት "እንደገና ተነቃቅቷል" ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ተናገሩ ቃለ አቀባዩ አርብ እለት ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሶማሊያ ሞቃዲሾ ያደረጉት ጉብኝት የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት አዲስ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ማሳያ ነው ብለዋል። አምባሳደር ነቢያት ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ያደረገችው ጥረት በተለይ በፖለቲካዊ ዲፕሎማሲ ማዕቀፍ ውጤታማ እንደነበር አንስተዋል። ሁለቱ ሃገራት ሽብርተኝነትን ለመዋጋት እና ለቀጣናዊና ዓለም አቀፍ ሰላምና ደህንነት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት ቁርጠኛ መሆናቸውንም ገልፀዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia