በደቡብ አፍሪካ የተካሄደው የቡድን 20 አባል ሀገራት የማዕከላዊ ባንክ ገዢዎች እና የፋይናንስ ሚኒስትሮች ስብሰባ ያለ ምንም የአቋም መግለጫ ተጠናቀቀተሳታፊዎቹ በብዙ ጉዳዮች ላይ መስማማት እንዳልቻሉ የጋራ መግለጫቸው አሳይቷል። ሆኖም በድን 20 በዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ትብብር ግንባር ቀደም ሚና እንደሚጫወት በድጋሚ ያረጋገጡ ሲሆን፤ በተጨማሪም በዓለም የኢኮኖሚ ልማት ዙርያ የሀሳብ ልውውጥ በማድረግ፤ ለዓለም ኢኮኖሚ ስጋት እየሆኑ የመጡ ጉዳዮችን በማስወገድ የባለብዙ ወገን ትብብርን ማጠናከር እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተዋል። ተሳታፊዎቹ የዓለም አቀፉ የፋይናንሺያል አርክቴክቸር ቡድን የስራ እቅድ ላይ የተወያዩ ሲሆን፤ የፋይናንስ ተግባር ግብረ ሃይል የባንክ ጥራት ደረጃ አፈፃፀምን በመቆጣጠር ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርን፣ ለአሸባሪዎች የሚደረግ የገንዘብ ድጋፍ እና የገንዘብ ድጋፍ መባዛትን ለመከላከል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ እንደሚደግፉ ገልጸዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia