በሩሲያ የተገነባው የግብፁ ኤል ዳባ ኤንፒፒ የኒውክሌር ጣቢያ አራት ተጨማሪ የኃይል ማመንጫዎችን የማስተናገድ አቅም እንዳለው የግንባታ ፕሮጀክት ዳይሬክተሩ ተናገሩ የኤል ዳባ ኤንፒፒ ፕሮጀክት ኃላፊ አሌክሲ ኮኖኔንኮ፤ በግብፅ አሌክሳንድሪያ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ዘላቂ የኒውክሌር ቴክኖሎጂ ፎረም የጎንዮሽ ውይይት ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ሩሲያ እና ግብፅ በኒውክሌር ኃይል ማመንጫዎች መስክ ያላቸው ትብብር እንደሚቀጥል ተስፋ አለኝ ብለዋል። ስለ ፎረሙ ሲናገሩ ኩነቱ ወጣቶች የኒውክሌር ኢነርጂ ቴክኖሎጂዎችን የበለጠ እንዲረዱ እድል እንደሚሰጣቸው በመጥቀስ፤ የመስኩን የወደፊት ተስፋ አንስተዋል። የግብፅ እና ሩሲያ ወጣቶች በኤል ዳባ ኤንፒፒ ፕሮጀክት ላይ እንዲሰሩ በስፋት እየተመለመሉ እንደሆነና በአዳዲስ ልዩ ትምህርቶች እየሰለጠኑ እንደሚገኙ አክለው ተናግረዋል። የግብፅ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ሊቀመንበር መሐመድ ድዊዳር፤ በኤል ዳባ ኤንፒፒ ፕሮጀክት ላይ ያለው ትብብር አወንታዊ ውጤት እያስገኘ መሆኑን ለስፑትኒክ ገልጸዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia