ናይጄሪያ የመጀመሪያ ዙር የትራክተሮች እና የግብርና ማሽነሪዎች ጭነት ከቤላሩስ ተረከበች ናይጄሪያ በአጠቃላይ 2 ሺህ ትራክተሮች እና 9 ሺህ 27 የግብርና ማሽነሪዎችን የተረከበች ሲሆን፤ ይህም ባለፈው ዓመት መስከረም ወር ላይ የተፈረመው የአቅርቦት ስምምነት አካል ነው ሲሉ የናይጄሪያ የግብርና እና የምግብ ዋስትና ሚኒስትር አቡበከር ኪያሪ ተናግረዋል። ሚኒስትሩ ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ወደ ሚንስክ ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ፤ ናይጄሪያ እና ቤላሩስ ከ2024-2029 የሚቆይ በግብርና እና የምግብ ዋስትና ዘርፍ ትብብራቸውን የማጠናከር ዓላማ ያለው ተግባራዊ እቅድ ተፈራርመዋል። ስምምነቱ የግብርና ማሽነሪዎች እና የምግብ ምርቶችን ለናይጄሪያ ማቅረብን ያካትታል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia