ኒጀር የነዳጅ ምርት ገቢዋን በአራት ዓመት ውስጥ በሶስት እጥፍ እንዳሳደገች ገለፀች

ኒጀር የነዳጅ ምርት ገቢዋን በአራት ዓመት ውስጥ በሶስት እጥፍ እንዳሳደገች ገለፀች ሀገሪቱ በ2020 ካስገባችው 102 ሚሊዮን ዶላር የነዳጅ ገቢ ጋር ሲነፃፀር፤ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት ከ320 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቷን የኒጀር የነዳጅ ዘይት ሚኒስትር ሳሃቢ ኡማሩ ገልፀዋል። የኒጀር መንግሥት ከነዳጅ አውጭ ኩባንያዎች ጥምረት ጋር በመሆን 112 የነዳጅ ዘይት ማውጫዎችን ማልማቱ እንዲሁም 1፣950 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው የነዳጅ ማስተላለፊያ ቦንቧ መገንባቱ ለነዳጅ ምርት እድገቱ በምክንያትነት ተጠቅሷል። በተጨማሪም 462.5 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው ሌላ የነዳጅ ማስተላለፊያ እንደተዘረጋ ተገልጿል። የነዳጅ ሀብቷን ከ13 ዓመት በፊት ማውጣት የጀመረችው ኒጀር፤ "ጥሩ ተስፋ" እንዳላት ኡማሩ ተናግረዋል። ኒጀር የነዳጅ ሀብት አቅሟን መጠቀም የሚያስችላት አጠቃላይ የሕግ፣ የቁጥጥር እና የኮንትራት ማዕቀፍ ተግባራዊ ማድረጓንም ጠቅሰዋል። የሀገሪቱ ነዳጅ ከበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ጋር የኢነርጂ ዘርፍ የትስስር ስምምነት እንድታደርግ ቁልፍ ሚና ተጫውቷል ተብሏል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik