ሩሲያ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት በአፍሪካ የነበረው የወጪ ንግዷ በ15% ማደጉ ተነገረ ከሩሲያ የጉምሩክ አገልግሎት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፤ ሩስያ ከአፍሪካ ጋር ባለፈው ዓመት የነበራት አጠቃላይ የወጪ ንግድ መጠን 24.3 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የነበረ ሲሆን፤ ከቀደመው ዓመት 21.2 ቢሊዮን ዶላር የወጪ ንግድ ገቢ ጋር ሲነፃፀር ከሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ ብልጫ አሳይቷል። በአጠቃላይ የሩሲያ የወጪ ንግድ በ2023 ከነበረው 425.3 ቢሊዮን ዶላር ጋር ሲነፃፀር፤ የባለፈው ዓመት የ2 በመቶ ጭማሪ አሳይቶ 433.9 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል። ከሩሲያ የወጪ ንግድ 76 በመቶ የሚሆነውን የምትቀበለው እስያ፤ የሞስኮ ግንባር ቀደም አጋር ሆና ቀጥላለች። ሩሲያ ወደ አውሮፓ በተመሳሳይ ወቅት የላከችው ምርት በ20 በመቶ ጭማሬ አሳይቷል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia