የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በቅርቡ ባሳለፈው የውሳኔ ሃሳብ ላይ የተካሄደው ድምጽ አሰጣጥ የፈረንሳይ እና እንግሊዝን ቅንነት ጥያቄ ውስጥ ከቷል ሲሉ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ገለፁ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በቅርቡ ባሳለፈው የውሳኔ ሃሳብ ላይ የተካሄደው ድምጽ አሰጣጥ የፈረንሳይ እና እንግሊዝን ቅንነት ጥያቄ ውስጥ ከቷል ሲሉ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ገለፁስኞ ተካሂዶ በነበረው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ዩናይትድ ስቴትስ በዩክሬን ጉዳይ ፀረ-ሩሲያ አቋም ያልተንፀባረቀበት የውሳኔ ሀሳብ ብታቀርብም፤ ብሪታንያ እና ፈረንሳይን ጨምሮ የአወሮፓ ሕብረት ሀገራት ፅሁፉን በማሻሻላቸው አሜሪካ ድምፀ ተአቅቦ እንድታደርግ ምክንያት ሆኗል። ከሰዓታት በኋላ አሜሪካ የመጀመሪያውን ረቂቅ ለተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት አቅራባ ምንም አይነት ለውጥ ሳይደረግበት አልፏል። ድምፅን በድምፅ የመሻር ሥልጣን የያዙት ፈረንሳይ እና ብሪታንያ፤ የውሳኔ ሐሳቡ ሳይሻሻል እንዲያልፍ ፈቅደዋል።ቃለ አቀባይዋ ማሪያ ዛካሮቫ ፈረንሳይ እና ብሪታንያ በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ የውሳኔ ሃሳቡ እንዲሻሻል አድርገው፤ በፀጥታው ምክር ቤት ግን ያለ ምንም ለውጥ ማፅደቃቸው ቅንነታቸው ላይ ጥያቄ እንደሚያስነሳ በመግለፅ፤ "በእያንዳንዱ ኪስ ውስጥ የተለየ ጭንብል አላቸው" ብለዋል።በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀደቁት ሁለቱም ውሳኔዎች በ93 ድምጾች እንደፀደቁ አስታውሰው፤ ይህ በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ አስቸኳይ ልዩ ስብሰባ ታሪክ እጅግ ዝቅተኛው ድምፅ እንደሆነ አስታውቀዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik