ሌኒንግራድ ከከበባ የወጣችበትን 81ኛ ዓመት መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ በደቡብ አፍሪካ አውደ ርዕይ ተከፈተ አውደ ርዕዩን ያዘጋጁት በሩሲያ ፕሬዝደንት ሥር የሚተዳደረው ብሔራዊ የታሪክ ማስታወሻ ማዕከል፤ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሩሲያ ፌዴሬሽን ቋሚ ተልእኮ ጋር በመተባበር ነው።በኬፕ ታውን የሚገኘው የሩሲያ ቆንስላ ጽ/ቤት ከካስትል ኦፍ ጉድ ሆፕ ጋር በመሆን በከፈተው አውደ ርዕይ፤ የሀገር ውስጥ በጎ ፈቃደኞች፣ የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ ወታደራዊ ክንፍ የቀድሞ ታጋዮች እና የድል በጎ ፈቃደኞች በመክፈቻው ፕሮግራም ላይ ተገኝተዋል። እ.አ.አ መስከረም 8፣ 1941 የጀርመን ናዚ ጦር ሌኒንግራድን (የአሁኗን ሴንት ፒተርስበርግ) መክበብ ጀመረ። በከተማዋ ረሃብ ያስከተለው ይሄ ከበባ 650 ሺህ የሚጠጉ ሰላማዊ ዜጎችን ለሞት የዳረገ ሲሆን፤ ጥር 18 ቀን 1943 ከበባው ከተሰበረ በኋላ ከተማዋ በጥር 27፣ 1944 ከከበባው ሙሉ በሙሉ ነፃ ወጥታለች።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia