የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከቱርክ አቻቸው ጋር በአንካራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ያነሷቸው ቁልፍ ሀሳቦች፦ የሩሲያ-አሜሪካ ግንኙነት፦ 🟠 በሪያድ የተካሄደው ስብሰባ ከአሜሪካ ጋር መደበኛ ውይይት እንደሚጀመር ተስፋ ሰጥቷል። 🟠 ሞስኮ እና ዋሽንግተን በዚህ ሳምንት የኤምባሲዎችን መደበኛ ስራ በተመለከተ ሙሉ ምክክር ያደርጋሉ። ዩክሬን፦ 🟠 ዘለንስኪ አቋሙን "ከአረንጓዴ ሸሚዞቹ የበለጠ" ይለዋውጣል። 🟠 ሞስኮ በዩክሬን ያለውን ግጭት የምታቆመው ድርድሩ ተጨባጭ እና ዘላቂነት ያለው ውጤት ሲያመጣ ብቻ ነው። 🟠 ከዩክሬን ጋር በሚደረገው ድርድር ኪዬቭ ኔቶን እንደማትቀላቀል የሚገልፅ "ተጨባጭ" ስምምነት ሊኖር ይገባል። 🟠 የሚቀጥለውን እርምጃ በሂደት ለማሰብ በሚል ከዩክሬን ጋር "በፍጥነት" ሰላም የመፍጠር አማራጭ ለሩሲያ አጥጋቢ አይሆንም። 🟠 ፕሬዝዳንት ትራምፕ ዩክሬንን ወደ ኔቶ መቀላቀል ስህተት እንደነበር ተቀብለዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia