ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያ ድጋፍ እና ማረጋጋት ተልዕኮ ውስጥ የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል ምደባን በተመለከተ ስምምነት ላይ ደረሱ

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያ ድጋፍ እና ማረጋጋት ተልዕኮ ውስጥ የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል ምደባን በተመለከተ ስምምነት ላይ ደረሱ በጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የተመራ ልዑክ በትናንትናው እለት በሶማሊያ የሥራ ጉብኝት አድርጓል፡፡ ጉብኝቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ መሃሙድ፤ በሞቃዲሾ የቴክኒክ ውይይት እንዲደረግ ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት የተደረገ ነው። ልዑኩ ከሶማሊያ ብሔራዊ ጦር ኃይሎች የመከላከያ ሰራዊት አዛዥ ሜጀር ጀነራል ኦዳዋ ዩሱፍ ራጌ ጋር በቀጣናው ስላለው የፀጥታ ሁኔታ ሀሳብ ተለዋውጧል።ሜጀር ጀነራል ኦዳዋ ዩሱፍ ራጌ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ለሶማሊያ መረጋጋት መስዋዕት እንደከፈለ በውይይቱ ወቅት ተናግረዋል። በተጨማሪም ሁለቱ ወገኖች በአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያ ድጋፍ እና ማረጋጋት ተልዕኮ ውስጥ የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል የሚኖረውን ተሳትፎ በተመለከተ ስምምነት ላይ ደርሰዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik