የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዝዳንት ዩክሬን ያለ አሜሪካ "ቸርነት" አትኖርምና፤ ፕሬዝዳንት ትራምፕን መንቀፍ "ሞኝነት" ነው ሲሉ ተናገሩ "የእርሱ (ቮሎድሚር ዜሌንስኪ) ሀገር ያለ ዩናይትድ ስቴትስ ቸርነት መኖር አትችልም። ስለዚህ እናመሰግናለን ነው የሚባለው፤ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር የማትስማማ ከሆነ ለፕሬዝዳንቱ ስልክ ደውል ወይም ለአንዱ ከፍተኛ ዲፕሎማት ደውል። በመላው አውሮፓ በየሚዲያው እየዞሩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንትን ስም ማጥፋት ግን አግባብ አይደለም። ይሄ ንቀት ነው...ይሄ ብልግና ነው" ሲሉ ጄዲ ቫንስ ተናግረዋል። በፕሬዝዳንት ትራምፕ የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች ዙርያ እሮብ እለት ምላሽ የሰጡት ዜሌኒስኪ፤ ፕሬዝዳንቱ በ "ሩሲያ የተሳሳተ መረጃ" ዓለም ውስጥ ሳይኖሩ አይቀሩም ሲሉ ተናግረዋል። ቫንስ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ዜሌኒስኪ በትራምፕ ላይ የሚያራምዱት "የስም ማጥፋት" ታክቲክ፤ ለዩክሬን አሉታዊ ውጤት ከማምጣት ባለፈ የሚፈይደው ነገር የለም ብለዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia