በኢትዮጵያ አየር መንገድ ይቋቋማል ተብሎ የነበረው የናይጄሪያ ብሔራዊ አየር መንገድ በድጋሚ ሊጀመር እንደሚችል ዘገባዎች ጠቆሙ ፕሮጀክቱን የጠነሰሱት የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ሙሐማዱ ቡሀሪ ሲሆኑ፤ መንግሥት መቀየሩን ተከትሎ ግን ውጥኑ እንደተጨናገፈ የናይጄሪያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚመራ ጥምረት፤ የናይጄሪያ ኤር 49% ድርሻን ይቆጣጠራል ተብሎ ይጠበቅ ነበር። ይሁን እንጂ የናይጄሪያ የአቪዬሽንና ኤሮስፔስ ልማት ሚኒስትር ፌስቱስ ኬያሞ፤ የፕሮጀክቱን ስምምነት በጽኑ ይተቹ እንደነበር ነው የተነገረው። ሆኖም ሚኒስትሩ ባሳለፍነው ሳምንት አዲስ አበባ መጥተው እንደነበርና ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው ጋር እንደተወያዩ ተገልጿል። ፐንች የናይጄሪያ ዜና አውታር ሚኒስትሩ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ሥራ አስፈፃሚ ጋር ፕሮጀክቱን በድጋሚ ሰለመጀመር ተወያይተው እንደነበር ተጠይቀው በአሉታዊው መልሰዋል ሲል ዘግቧል። ሰነዶችን ያጣቀሰው የፐንች ዘገባ ግን፤ የናይጄሪያ ብሔራዊ አየር መንገድ ፕሮጀክትን በአዲስ ስያሜ የማስጀመር እቅድ ሊኖር እንደሚችል ጠቁሟል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia