የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሩሲያ ላይ የተጣሉ የአውሮፓ ኅብረት እና የአሜሪካ ማዕቀቦች ሊነሱ ይችላሉ አሉ "አውሮፓውያን እና የአውሮፓ ኅብረት በሩሲያ ላይ የራሳቸው የሆነ ማዕቀብ አላቸው። በሳዑዲ አረቢያ ስለ ማዕቀብ ማንሳት ባናወራም፤ ሁሉንም ማዕቀብ የምናነሳ ከሆነና ነገሮች እንዲሰምሩ አውሮፓውያንም ማዕቀቡን ማንሳት አለባቸው። በዚያ ደረጃ ላይ ባንሆንም በተወሰነ መልኩ የሆነ ወቅት ላይ እነሱን ማማከር ይኖርብናል" ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርኮ ሩቢዮ ከጋዜጠኛ ካትሪን ሄሪጅ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ ተናግረዋል። በሳዑዲ አረቢያ የነበሩት የአሜሪካ እና የሩሲያ ልዑካን "የስብሰባው አላማ ስላልነበር" "ግዛቶችን የተመለከተ ምንም ዓይነት ዝርዝር ውይይት አላካሄዱም" ሲሉም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል። እንደ ሩቢዮ ገለጻ አሜሪካ እና ሩሲያ ስምምነት ላይ ሊደርሱ በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ወይም ሊፈጠሩ የሚችሉ አደጋዎችን መቀነስ ላይ ሊሰሩ ይችላሉ።"በብዙ ጉዳይ ላይ አንስማማም። ነገር ግን ልንስማማ በምንችላቸው ነገሮች ላይ መስራት ወይም ወደ አደገኛ ግጭቶች ሊያመሩ በሚችሉ ነገሮች ላይ መካረርን መቀነስ የሚያስችል ስራ መስራት እንችላለን፤ ይህ የዩክሬን ጉዳይ መሰናክል ፈጥሮ እንቅፋት እስካልሆነብን ድረስ" ሲሉ አብራርተዋል። ሩሲያ በዓለም ቁልፍ ቦታዎች ላይ ተጽእኖዋን የምታሳድር፤ ዓለም አቀፋዊ ኃይል እንደሆነችም ሚኒስትሩ አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia