የሩሲያ ዩኒቨርስቲዎች ከምዕራብ አፍሪካ ተቋማት ጋር ለመተባበር ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው የሕዝብ ዲፕሎማሲ ማዕከል ኃላፊ ተናገሩ "25 ዩኒቨርሲቲዎችን ያካተተ እና ሁሉንም የትምህርት ዘርፎች የሚወክል የሩሲያ ዩኒቨርሲቲዎች ጥምረት ፈጥረናል። ይህም በመጀመርያ ድግሪ፣ በማስተርስ እና በድህረ ምረቃ ነው። የሩሲያ ዩኒቨርሲቲዎች ምዕራብ አፍሪካ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው" ሲሉ የሕዝብ ዲፕሎማሲ ማዕከል ዳይሬክተር ናታሊያ ክራሶቭስካያ ተናግረዋል። ዳይሬክተሯ ይህን ያሉት በትምህርት፣ ሳይንስ፣ ኢኮኖሚ እና ባህል ላይ ትኩረቱን ባደረገውና በኒጀር ዋና ከተማ ኒያሚ በተካሄደው ዓለም አቀፍ ፎረም ላይ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው። በፎረሙ ላይ የተሳተፈው የሩሲያ ልዑክ በሦስት ዋና ዋና የሩሲያ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ሁለት ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እና በተጨማሪ ዘርፎች እንደተወከለ ክራሶቭስካያ ገልፀዋል። "ስራው እየሰፋና እየተጠናከረ ሲሄድ የሩሲያ ዩኒቨርሲቲዎች ኒጀርን በአካል ለመጎብኘት እና የኒጀር ዩኒቨርሲቲዎችን በግል ለማወቅ ከፍተኛ ፍላጎት አሳይተዋል" ብለዋል። በፎረሙ የሕዝብ ዲፕሎማሲ ማዕከል እና የሩሲያ ዩኒቨርስቲዎች ጥምረት ለኒጀር ኢኮኖሚ አጠቃላይ የትምህርት ፕሮግራም ሃሳብ አቅርበው ወይይት ተደርጎበታል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia