ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር ኢኮኖሚያዊ ትብብር ለመፍጠር ፍላጎቷን ገልጻለች ሲሉ የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ቫለንቲና ማትቪዬንኮ ተናገሩ የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤዋ በመጨረሻ ቀን የአዲስ አበባ ጉብኝታቸው ከኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ ከተገናኙ በኋላ ባወጣው መግለጫ "ጉብኝቱ ፍሬያማ ነበር፤ ተጨባጭ ስምምነቶችን አስገኝቷል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ (ቫለንቲና ማትቪዬንኮ) ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር በፓርላማ እንዲሁም በንግድና ኢኮኖሚ ዘርፎች ትብብር ለማድረግ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት አረጋግጣልናለች ብለዋል" ሲል አስታውቋል።አፈ ጉባኤዋ ሞስኮ ከአዲስ አበባ ጋር የንግድ እና የኢኮኖሚ ትብብሯን ለማሳዳግ ፍላጎት እንዳላት በመግለፅ፤ ኢትዮጵያ በግብርና፣ በታዳሽ ኃይል፣ በማዕድን፣ በኢንፎርሜሽን እና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂዎች እና ቱሪዝም ትልቅ አቅም እንዳላት አንስተዋል። ማትቪዬንኮ በኢንተር ፓርላማ ህብረት እና ብሪክስ ማዕቀፍ ውስጥ ከኢትዮጵያ ጋር ውጤታማ ግንኙነት እንዳለም አጽንኦት ሰጥተዋል። "ሩሲያ ኢትዮጵያ ወደዚህ ስብስብ እንድትቀላቀል ከፍተኛ ድጋፍ አድርጋለች፤ የኢትዮጵያውያን አጋሮቻችን ትጋትና ውጤታማ እንቅስቃሴ አይተናል፤ ሀገሪቷ ለስብስቡ የጋራ ጥንካሬ አስደናቂ አስተዋጽኦ እያበረከተች ትገኛለች፤ አባላቶቹ የአፍሪካ አህጉርን በተመለከተ አዲስ እይታን እንዲያገኙ አድርጓል። ብሪክስ አዲስ፣ ጠንካራ እና ንቁ አባል አግኝቷል" ብለዋል ማትቪዬንኮ።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia