የኢትዮጵያን ቦንድ የገዙ ኢንቨስተሮች ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ሁኔታ አስመልክቶ በቅርቡ ያወጣውን ሪፖርት አንቀበልም አሉ ሀገሪቱ እዳዋን መክፈል አትችልም ያለው የአይኤምኤፍ ሪፖርት “ጉልህ ጉድለቶች” አሉበት ብለዋል። የኢትዮጵያ አባዳሪዎች ኮሚቴ፤ የአይኤምኤፍ የባለሙያ ቡድን በሪፖርታቸው ላይ በደረሱት ድምዳሜ እንደማይስማሙ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ሪፖርቱ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዙርያ ያቀረበው ግምት ኮሚቴው ካካሄደው ግምገማ ጋር እንደማይጣጣም፤ የኮሚቴው መግለጫ አመላክቷል። የባለሙያዎቹ ሪፖርት የኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚ በከፍተኛው እንደተሻሻለ ግምት ውስጥ ሳያስገባ ቀርቷል ያለው መግለጫው፤ የሀገሪቱን ቁልፍ የወጪ ንግድ ዘርፎች የገበያ ዋጋ አሳንሶ ገምቷል ብሏል። ከኢትዮጵያ የ1 ቢሊዮን ዶላር ቦንድ ከ40% በላይ ድርሻ ያላቸውን ባለሀብቶች የሚወክለው ኮሚቴ፤ ዕዳውን ለማስከፈል የፍትህ አማራጮችን የመጠቀም መብት እንዳለው ጠቁሟል ሲል የምዕራቡ ዓለም መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia