የሩሲያ እና አሜሪካን ግኑኝነት ወደ ነበረበት ለመመለስ እና የዩክሬንን ጉዳይ ለመፍታት የሚካሄደው ንግግር ቀጥሏል እስካሁን የታወቁ ጉዳዮች፦ 🟠 ስብሰባው ለመገናኛ ብዙሃን ቅድመ መግለጫ በመስጠት ተጀምሯል። 🟠 በሩሲያ በኩል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ እና የሩሲያ ፕሬዝዳንት አማካሪ ዩሪ ኡሻኮቭ በድርድሩ ላይ ተገኝተዋል። 🟠 በአሜሪካ በኩል የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚካኤል ዋልትዝ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ እና የመካከለኛው ምስራቅ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ተገኝተዋል። 🟠 ከአሜሪካ ጋር የሚደረገው የኢኮኖሚ ድርድር ከ2 እስከ 3 ወራት መሻሻሎችን ሊያመጣ ይችላል ሲሉ በመካሄድ ላይ ያለውን ድርድር የኢኮኖሚ ክፍል የሚመሩት የሩሲያ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፈንድ ኃላፊ ኪሪል ዲሚትሪቭ ገልጸዋል። 🟠 በድርድሩ ወቅት የሩሲያ ተሳታፊዎች የአሜሪካ ባልደረቦቻቸውን ያዳምጣሉ የተባለ ሲሆን በቀጣይ እርምጃዎች ዙርያ ፑቲን እና ትራምፕ ውሳኔ እንደሚሰጡ ይጠበቃል። ውይይቱ የሳዑዲ ባለስልጣናት ልዑካንን እና የውጭ ሀገር እንግዶችን ለመጋበዝ በሚመርጡት አድ-ዲሪያ ቤተ-መንግሥት በመካሄድ ላይ ይገኛል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia