ከብሪክስ ጋር በምትፈጥረው ጠንካራ ግኑኝነትት ተጠቃሚ መሆን እንደምትፈልግ የናይጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ የናይጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዩሱፍ ቱጋር "በርካታ የቅርብ የንግድ አጋሮቻችንን ያቀፈውን የብሪክስ ስብስብ እየተቀላቀልን ያለነው፤ እንደ አጋር እንጂ እንደ አባል አይደለም። ለማሳያ ከብራዚል እንዲሁም ከሩሲያ ጋር የቆየ ግንኙነት አለን። ህንድ ጠንካራ የንግድ አጋራችን ነች፤ ቻይናም ብትሆን አሁን ላይ ትልቋ የናይጄሪያ የንግድ አጋር ነች፤ ደቡብ አፍሪካ ደግሞ እህት ሀገር ናት" ሲሉ በ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ወቅት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ናይጄሪያ ከጥር ወር ጀምሮ ከቤላሩስ፣ ቦሊቪያ፣ ኩባ፣ ካዛኽስታን፣ ማሌዥያ፣ ታይላንድ፣ ኡጋንዳ እና ኡዝቤኪስታን በመቀጠል የብሪክስ አጋር ሀገር መሆን እንደቻለች የብራዚል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia