የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ገበያ እና የሩዋንዳ ስቶክ ኤክስቼንጅ የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ

የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ገበያ እና የሩዋንዳ ስቶክ ኤክስቼንጅ የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ ስምምነቱን የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ገበያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጥላሁን እስማዔል እና የሩዋንዳ ስቶክ ኤክስቼንጅ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፒዬር ሴሌስቲን ራዋቡኩምባ ተፈራርመዋል። "ይህ የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ቀጣናዊ ትስስርን የማጠናከር ሚናን ይጫወታል። የሁለቱን ካፒታል ገበያዎች ጥንካሬ በመጠቀም ኢንቨስተሮችን እና ቢዝነስን የሚጠቅም ተለዋዋጭ እና እርስ በእርስ የተሳሳረ ካፒታል ገበያን ለመፍጠር እንጥራለን " ሲሉ የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ገበያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጥላሁን እስማዔል ተናግረዋል። ስምምነቱ በሀገራቱ መካከል ያለውን ትብብር እና የምሥራቅ አፍሪካን የገበያ ልማት የሚያጠናክር ነው ተብሏል። የሩዋንዳ ስቶክ ኤክስቼንጅ ዋና ስራ አስፈፃሚ በበኩላቸው "ይህ ፊርማ የሁለቱን ካፒታል ገበያዎች ለማጠናከር፣ ለእውቀት መጋራት እና ለፈጠራ ያለንን ቁርጠኝነት፤ እንዲሁም ለሁለቱም ተቋማት እና ለማህበረሰቦቻችን የሚጠቅሙ ጠንካራ አጋርነት ለማጎልበት አስፈላጊ እርምጃ ነው" ብለዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik