የአፍሪካ ሀገራት በተፈጥር ሀብታቸን ላይ የሚደረገው ስርዓታዊ ብዝበዛ እንዲቆም እንጠይቃለን ሲሉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ "የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ በሀብት፣ ንብረት እና ዕድሎቻችን ላይ የሚፈፀመው ብዝበዛ እንዲቆም ይጠይቃል" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ በሚገኘው 38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተናግረዋል። "የማካካሻ ፍትህ ለአፍሪካውያን እና ለትውልደ አፍሪካውያን" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ያለው ጉባዔ፤ አፍሪካውያን "በታሪክ ከደረሰባቸው በደል እንዲያገግሙ እንዲሁም የአህጉሪቱን እድገት ወደ ኋላ ሲጎትት የቆየውን ጥፋት አሸንፈው እንዲወጡ" ጥሪ ያቀርባል ብለዋል። የማካሻሻ ፍትህ እርዳታ ሳይሆን ክብርን ለመመለስ፣ ድህነትን፣ ልዩነትን፣ መድልዎ፣ መገለልን እና የተፈጥሮ ሀብት ብዝበዛን ለመዋጋት የሚደረግ ነው ብለዋል። "የአፍሪካ ሕብረት ገባዔ ለበፊት ጉዳቶች እውቅና የሚሰጥ እና በእኛ እና በመላው የአህጉሪቱ ማህበረሰብ ላይ የደረሱ ስህተቶችን ለማረም ቁርጠኛ እርምጃ መውሰድ ለሚችል የለውጥ ሂድት ጥሪ ያቀርባል" ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia