አፍሪካ የምግብ ምርቷን ማሳደግ አለባት ሲሉ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽነር ተናገሩ "የመጀመሪያ ስትራቴጂካዊ ምሰሶአችን የሆነው የምግብ ዋስትና በዘላቂነት ለማረጋገጥ ምርታማነታችንን በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ ይኖርብናል። በ2050 የአፍሪካ ሕዝብ ቁጥር 2.5 ቢሊዮን ይደርሳል ተብሎ ይገመታል፤ እንዴት ነው ይህን ቁጥሩ እየጨመረ ያለ ህዝብ የምንመግበው? ለዚህም ነው ዘላቂ የምግብ ምርታማነትን ለማረጋገጥ ጠንክረን መስራት ያለብን" ሲሉ ተሰናባቿ የአፍሪካ ሕብረት የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የሰማያዊ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ አካባቢ ኮሚሽነር ጆሴፍ ሳኮ ተናግረዋል። ኮሚሽነሯ አክለውም የአፍሪካ ሀገራት የምግብ ማቀነባበር አቅማቸውን ማስፋፋት አለባቸው ብለዋል። እንደ ሳኮ ገለፃ፤ እነዚህን ስረዓቶች ማሻሻል አስፈላጊ የሚሆነው የምግብ ስረዓትን ለማረጋጋጥ ብቻ ሳይሆን፤ ቁጥሩ በፍጥነት እያደገ ለመጣው የአህጉሪቱ ወጣት የስራ እድል ለመፍጠርም ጭምር ነው ብለዋል። ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥ በግብርና ምርት ላይ የሚያመጣውን ተፅዕኖ ከግምት ውስጥ ማስገባት እንዲሁም በአፍሪካ በተደጋጋሚ የሚከሰተውን ድርቅ እና ሌሎች የተፈጥሮ አደጋዎች ለመቋቋም የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን መጠቀም እንደሚኖርባቸው አስገንዝበዋል። በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia