የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኒውክለር መካካርን ለማርገብ ከቻይና እና ሩሲያ አመራሮች ጋር እንደሚገናኙ አስታወቁ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር በጋራ በሰጡት መግለጫ ላይ ባደረጉት ንግግር "ከቻይና ጋር እገናኛለሁ፤ ከሩሲያም ጋር እገናኛለሁ፤ ወታደራዊ መካካርን በተለይም ከኒውክሌር ጋር በተያያዘ ማርገብ የምንችልበትን መንገድ እንመለከታለን" ብለዋል። ቻይና የዩክሬኑ ግጭት እንዲቆም ወሳኝ ሚና መጫወት ትችላለች ሲሉም የአሜሪካው ፕሬዝዳንት አክለዋል። "ቻይና በዓለም ላይ ወሳኝ ሚና ያላት ሀገር ናት ብዬ አስባለሁ። እኔ እንደማስበው የሩሲያ እና ዩክሬንን ጦርነት በማስቆም ልትረዳን ትችላለች" ብለዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia