ደቡብ አፍሪካ፣ ናሚቢያ፣ ቻይና እና ህንድ ቱሪዝምን ለማሳደግ እና ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ያለመ የቪዛ ፖሊሲ ማሻሻያ አደረጉ

ደቡብ አፍሪካ፣ ናሚቢያ፣ ቻይና እና ህንድ ቱሪዝምን ለማሳደግ እና ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ያለመ የቪዛ ፖሊሲ ማሻሻያ አደረጉ ደቡብ አፍሪካ ከቻይና እና ህንድ ተጨማሪ ቱሪስቶችን ለመሳብ ያለመ ተዓማኒ የአስጎብኚ ስርዓት የተሰኘ አሰራር አስጀምራለች። እርምጃው ከእነዚህ ቁልፍ ገበያዎች ለሚመጡ ጎብኚዎች የበለጠ ተደራሽ በመሆን ቱሪዝምን እንደሚያሳድግ፣ የስራ እድል እንደሚፈጥር እና የኢኮኖሚ እድገትን እንደሚያበረታታ ይጠበቃል። ሥራ ላይ የዋለው አዲስ ስርዓት ዘርፉ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለማስወገድ እና የጎብኚዎችን ቁጥር የመጨመር ግብም አንግቧል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ናሚቢያ የዲፕሎማሲያዊ እና ኦፊሴላዊ ፓስፖርት ለያዙ ቻይናውያን ከቪዛ ነፃ የጋራ የመግባቢያ ስምምነት አጽድቃለች። በተጨማሪም ከሌሎች ሀገራት ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ስምምነት ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለማጠናከር የቪዛ ፖሊሲዋን እያስተካከለች ትገኛለች።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik