ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ የንግድ መስመራቸውን የሚያስተዳድር ባለሥልጣን መሰረቱ ሁለቱ ጎረቤት ሀገራት በአስተዳደር ባለስልጣኑ ምስረታ ዙርያ በቴክኒክ ኮሚቴ ደረጃ ያካሄዱትን ውይይት እሮብ እለት አጠናቀዋል። በውይይቱም የኢትዮ-ጅቡቲ ኮሪደር አስተዳደር ባለስልጣንን ለመመስረት ተስማምተዋል። በሁለትዮሽ ረቂቅ የመመስረቻ ሰነድ ላይ የመከሩት ሁለቱ ሀገራት፤ ሂደቱ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለፊርማ ዝግጁ እንዲሆን ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን፤ በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ነው ያስታወቀው። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia