ፈጣን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ባትሪ መሙያ ጣቢያዎች በኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ ወደ ሥራ ገቡ ኢትዮቴሌኮም ወደ ሥራ ያስገባቸው ጣቢያዎች፤ እስከ 600 ኪሎ ዋት ድረስ ቻርጅ የማድረግ አቅም ያላቸው 8 እጅግ በጣም ፈጣን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ መሙያዎችን፣ እስከ 500 ኪሎ ዋት ድረስ ቻርጅ የማድረግ አቅም ያላቸው 12 በጣም ፈጣን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ መሙያዎችን እንዲሁም የድንገተኛ ባትሪ መሙያ ስማርት ምሰሶ ቻርጀሮችን ያካትታል። ዘመናዊው የኤሌክትሪክ መኪና ኃይል መሙያ በ1 ሰከንድ 1 ኪሎ ሜትር መጓዝ የሚያስችል ነው ተብሏል። እንደ ተሸከርካሪው አቅም በ15 ደቂቃ ውስጥ ሙሉ (100%) የኤሌክትሪክ ኃይል እንደሚሞላም ተገልጿል። የቻርጅ ጣቢያው ሰባቱንም ቀናት ለ24 ሰዓት አገልግሎት ይሰጣል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia