ደቡብ አፍሪካ ወታደሮቿን ከኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ “በድንገት ማስወጣት” እንደማትሻ ገለጸች "አንዳንድ የፓርላማ አባላቶች የሚያቀርቡት የመውጣት ሃሳብ ታክቲካዊ ማፈግፈግ እንኳን አይደለም፤ እጅ ከመስጠትም የከፋ ነው፤ በአካባቢው ካሉት የታጠቁ ሃይሎች ቁጥር አንጻር የድንገተኛ ጥቃት ስጋት አለ" ሲሉ የደቡብ አፍሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሮናልድ ላሞላ ተናግረዋል። እንደ ላሞላ ገለጻ፤ የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ እና የደቡባዊ አፍሪካ የልማት ማህበረሰብ ስብሰባ በግጭቱ አፈታት ዙሪያ ግልፅ መንገድ አስቀምጧል። በዚህ ሂደትም ፕሪቶሪያ “ተመልካች መሆን እንደማትችል” አስረግጠዋል። የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በወታደሮች ላይ ኪሳራ ቢደርስም፤ ለኮንጎ የሚያደርጉትን ድጋፍ "እንደማያቆሙ" ቀደም ብለው ተናግረዋል። ኤም23 አማጺ በድን በቅርቡ በምስራቅ ኮንጎ ባካሄደው ዘመቻ የደቡባዊ አፍሪካ የልማት ማህበረሰብ ልዑክ አባል የሆኑ 14 የደቡብ አፍሪካ ወታደሮች ተገድለዋል። ወታደሮቹ ከ2023 ጀምሮ በክልሉ ተሰማርተው እንደነበር ተገልጿል። ማላዊ ወታደሮቿን ከኮንጎ ምስራቃዊ ክፍል ማስወጣት መጀመሯን ጥር 30 ቀን አስታውቃለች።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia