የሩሲያ የዲፕሎማሲ ሰራተኞች ቀን " ዲፕሎማቶች ግንኙነት እንዲፈጥሩ እድል ይፈጥራል" በማለት የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ተናገሩ የሩሲያ ዲፕሎማቶች ፕሮፌሽናል በአላቸውን ፤ በሚዲያ ቻናሎች አማካኝነት ያላቸውን የአለምአቀፍ ግንኙነቶችን ግምገማ ውጤት በማጋራት ያከብራሉ ፤ በማለት ማሪያ ዛክሃሮቫ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።በተጨማሪም ቀኑ በሚዲያ ኩነቶች ፤ የዲፕሎማቲክ ተልእኮዎች በሚያዘጋጁት ሪሰፕሺን እና ከአለምአቀፍ ተመሳሳይ ድርጅቶች የእንኳን ደስአላችሁ መልእክት በመቀበል ይከበራል ብለዋል ቃል አቀባይዋ። " ነገርግን በዚህ የበአል አከባበር ወሳኝ የሆነ ነገር አለ ፤ ይህ ቀን ማክበር የምንጀምረው ለወደቁ ጓዶቻችን መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን በማስቀመጥ ነዉ። ይህ መታሰቢያ በታላቁ የአርበኝነት ጦርነት ላይ የተሳተፉ ዲፕሎማቶቻችንንም በሚገባ ያካትታል" በማለት ዛክሃሮቫ ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia