በኢትዮጵያ የተከፈተው አዲስ የፕላስቲክ ፎርምወርክ ፋብሪካ በዓመት ከ15 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ማስቀረት የሚችል መሆኑ ተገለጸ

በኢትዮጵያ የከፈተው አዲስ የፕላስቲክ ፎርምወርክ ፍብሪካ በየአመቱ ወደ ውጭ ይወጣ የነበረ 15 ሚሊዩን ዶላር ይቆጥባል ተባለይህ በስምንት ሚሊዩን ዶላር የተገነባውን የፎርምወርክ (ለግንባታ ሆነ ለሌሎች አገልግሎቶች የሚውል ምርት) ፍብሪካ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል መርቀውታል። በምርቃቱ ወቅት ሚኒስትሩ መንግስት ለአምራቹ ዘርፍ የሰጠውን ትኩረት አፅንኦት በመስጠት ለዚህም የሚያገለግል የፖሊሲ እና ለኢኮኖሚ እድገት የሚያግዝ የህግ ማእቀፍ ማሻሻያዎችን አድርጓል ፤ ይህም ምርታማነትን ማሳደግ እና ለዘላቂ ልማት የሚያግዝ እገዛን ማቅረብ ያካትታል ብለዋል።ሚኒስትሩ በሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎችን ማልማት ከውጭ ለሚገቡ ምርቶች ተለዋጭን ለመፍጠር ያገለግላል ፤ ይህም የኢትዩጵያን አረንጓዴ አሻራ የሚደገፍ እና ከእንጨት እና ከብረት የሚሰሩ ፎርምወርኮችን በፕላስቲክ የመቀየር ተነሳሽነት ነው።የኤችኬ ንግድ ቡድን ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ካሳነሽ አያሌዉ እንዳስታወቁት ድርጅታቸው በድጋሚ አገልግሎት ላይ የሚውል የፕላስቲክ ፎርምወርክ ምርት ለሀገረ ውስጥ እና የውጭ ገበያዎች አምርቶ ለማቅረብ ዝግጁ ነው ፤ ለዚህም አገልግሎት ከቻይና እና ከአደጉ ሀገራት ቴክኒዎሎጂዎችን ማስገባታቸውን ተናግራለች። ዋና ስራ አስኪያጇ አፅንኦት በመስጠት ከ 20 -25 በመቶ የሚሆነውን የግንባታ ወጪው የፎርምወርክን ይወክላል በማለት ፤ ፋብሪካው የሀገር ውስጥ እና የጎረቤት ሀገራትን የፎርምወርክ ፍላጎት በሚያሟላበት አቋም ላይ መሆኑን ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik
በኢትዮጵያ የተከፈተው አዲስ የፕላስቲክ ፎርምወርክ ፋብሪካ በዓመት ከ15 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ማስቀረት የሚችል መሆኑ ተገለጸበስምንት ሚሊዮን ዶላር የተገነባውን የፎርምወርክ ፋብሪካ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል መርቀውታል። ሚኒስትሩ በምርቃቱ ወቅት እንደተናገሩት መንግሥት ለአምራቹ ዘርፍ ትኩረት በመስጠት የፖሊሲ  እና ለኢኮኖሚ እድገት የሚያግዙ የህግ ማእቀፍ ማሻሻያዎችን ያደረገ ሲሆን፤ ይህም ምርታማነትን እና ዘላቂ ልማትን መደገፍ ያካትታል ብለዋል።ሚኒስትሩ የሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎችን  በማልማት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን መተካት እንዲሁም የኢትዮጵያን አረንጓዴ አሻራ ከእንጨት እና ከብረት የሚሰሩ ፎርምወርኮችን በፕላስቲክ በመቀየር መደገፍ እንደሚገባ ተናግረዋል።የኤችኬ ንግድ ቡድን ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ካሳነሽ አያሌዉ እንዳስታወቁት ድርጅታቸው በድጋሚ አገልግሎት ላይ የሚውል የፕላስቲክ ፎርምወርክ ምርት ለሀገረ ውስጥ እና የውጭ ገበያዎች አምርቶ ለማቅረብ ዝግጁ ነው። ለዚህም አገልግሎት ከቻይና እና ከአደጉ ሀገራት ቴክኒዎሎጂዎችን ማስገባታቸውን ተናግረዋል። ዋና ስራ አስኪያጇ ፎርምወርክ ከ20 -25 በመቶ የሚሆነውን የግንባታ ወጪ እንደሚወክል በመግለፅ፤ ፋብሪካው የሀገር ውስጥ እና የጎረቤት ሀገራትን የፎርምወርክ ፍላጎት በሚያሟላበት አቋም ላይ መሆኑን ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia