የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቡድን ዋና ስራ አስፈፃሚ በጋና በተካሄደ ሥነ-ሥርዓት ተሸላሚ ሆኑ አፍሪካን በአየር ትራንስፖርት በማገናኘት ረገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እየተጫወተ ላለው ሚና ላሳዩት የላቀ የአመራርነት ሚና የተበረከተውን ሽልማት በጋና አክራ በመገኘት ተረክበዋል። ሽልማቱ የተበረከተላቸው በአፍሪካ ሁለንተናዊ እድገትና ብልፅግና ላይ ትኩረቱን ባደረገው የ '2025 የአፍሪካ ፕሮስፔሪቲ ዲያሎግ' መድረክ ላይ ነው።መድረኩ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች፣ የአህጉሪቱ ግዙፍ የንግድ ተቋማት ተወካዮች፣ መሪዎች እና ተፅእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በተገኙበት ተካሂዷል። ይህ ሽልማት አፍሪካን እርስ በእርስ ለማገናኘት ወሳኝ አመራር እና ሚና ለተወጡ ግለሰቦች እውቅና የሚሰጥበት እንደሆነ አየር መንገዱ አስታውቋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia