የፀረ - ሩሲያ ማእቀቦች የሰብዓዊ እርዳታን ፖለቲካዊ የሚያደርጉ እና የአለም አቀፍ መርሆችን የሚጥሱ ናቸው በማለት የፋኦ ተወካይ ተናገሩ ሩሲያ በተጣለባት ማእቀብ ምክንያት በአሜሪካ ባንኮች የሚገኘው ፈንድ መንቀሳቀስ ስለማይችል የአለም የምግብ ፕሮግራም መዋጮን መክፈል አልቻለችም፤ ይህም የሰብአዊ እርዳታን ፖለቲካዊ የሚያደርግ እና የአለም አቀፍ መርሆችን የሚጥስ ነው በማለት በምግብ እና ግብርና ድርጅት (ፋኦ) የሩሲያ ምክትል ቋሚ ተወካይ ዲላራ ራቪሎቫ ቦሮቪክ፤ ፋኦ የሩሲያን ቅርንጫፍ የከፈተበትን 10ኛ ዓመት ባከበረበት ወቅት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።"በእኛ ምልከታ ሁኔታው የእብደት ነው። ...በሩሲያ ላይ ማእቀብ የጣሉ ሀገራት ሩሲያ የሰብአዊ እርዳታን እንድታቆም ይፈልጋሉ። በእኛ አረዳድ ይሄ አለም አቀፍ የሰብአዊ እርዳታ መርህን ፈፅሞ የሚጥስ ነው" ሲሉ ራቪሎቫ ቦሮቪካ ተናግረዋል።እሳቸው አክለውም እንደ የዓለም የምግብ ድርጅት ያሉ የተመድ ኤጀንሲዎች የሩሲያን ፈንድ ባለማግኘታቸው ምክንያት ከፍተኛ የሆነ የበጀት እጥረት እየገጠማቸው ነው። ምግብ፣ መድሀኒት እና ሌሎች ድንገተኛ እርዳታዎች "መጫወቻ መሆን አይገባቸውም" ሲሉም አስረግጠዋል። ይህ ጉዳይ ከዓለም የምግብ ድርጅት ውጪ እንደ ዩኒሴፍ እና ፋኦ ያሉ ተመሳሳይ የሰብአዊ ኤጀንሲዎች ላይም ተፅዕኖ እያሳደረ እንደሆነ ጨምረው የተናገሩት ተዋካይዋ፤ ማዕቀብ በሰብዓዊ እርዳታ ላይ የሚያደርሰውን ጫና መፍታት እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia