ዋሽንግተን የጋዛን ነዋሪዎች ወደ ሞሮኮ እና ሶማሊያ ለማዘዋወር እያሰበች መሆኑን ሪፖርቶች አመለከቱ ዋሽንግተን የጋዛ ነዋሪዎችን ሱማሊያ ውስጥ ራስ ገዝ ክልሎች ወደሆኑት እና ነፃነታቸውን ቢያውጁም በአለም አቀፍ ህብረተሰብ ዘንድ እውቅና ወዳልተሰጣቸው ሶማሌላንድ እና ፑትላንድ እንዳሁም ወደ ሞሮኮ ለማዘዋወር እያጤነች እንደሆነ የእስራኤሉ ኤን 12 የዜና ማሰራጫ ዘግቧል። ሁለቱ የሱማልያ ራስ ገዝ ክልሎች አለም አቀፍ እውቅናን ለማግኘት፤ ሞሮኮ በበኩሏ ምእራብ ሰሃራ ላይ ያላትን የግዛት ጥያቄ ለመፍታት የአሜሪካን የፖለቲካ ድጋፍ እንደሚፈልጉ እና ሶስቱም ጋር ሱኒዎች በቁጥር አብላጫውን እንደሚይዙ ማሰራጫው ጨምሮ ዘግቧል።የዋሽንግተን ጋዛን የማስለቀቅ እና መልሶ የመገንባት እቅድ ሰርጡን ወደ ነበረበት ለመመለስ እንጂ ዩናይትድ ስቴትስ ግዛቱን የመጠቅለል ዓላማ የላትም ሲል ዘገባው አክሏል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia