የሩዋንዳ እና የሩሲያ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች በኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ውስጥ ያለውን ሁኔታ አስመልክቶ ተወያዩየሩዋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦሊቪር ንዱሁንጊሬህ እና የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚክሃል ቦግዳኖቭ የስልክ ውይይት አካሂደዋል። "በውይይታቸው የሩዋንዳ - ሩሲያን ትብብር ስለማጠናከር እና በምስራቅ ኮንጎ ስላለው ሁኔታ መክረዋል" ሲል የሩዋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት አስታውቋል። የስልክ ውይይቱ " ውጤታማ" እንደነበር ሚኒስቴሩ ገልጿል።የኮንጎ መንግሥት ሩዋንዳ በምስራቁ የሀገሪቱ ክፍል የሚንቀሳቀሱትን አማፂያን ትደግፋለች የሚል ክስ የሚያቀርብ ሲሆን፤ በተጨማሪም ወታደሮቿን ከኮንጎ ግዛት እንድታስወጣ ጠይቋል። ሩዋንዳ ሁሉንም ክሶች ውድቅ አድርጋለች።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia