የዩኤስ ኤአይዲ የባህር ማዶ ቢሮዎች እንዲዘጉ እና ሰራተኞቹ እስከ አርብ ድረስ ለቀው እንዲወጡ ትእዛዝ እንደተሰጣቸው ተሰማ የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት ምክትል አስተዳዳሪ ሆነው የተሾሙት ፒት ማሮኮ፤ ማክሰኞ እለት ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባለስልጣናት ጋር እንደተገናኙ እና የዩኤስ ኤአይዲ ሰራተኞች እስከ አርብ ድረስ ከየተመደቡበት ሀገር ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ መስጠታቸውን ምንጮቹን ጠቅሶ ሲቢኤስ ኒውስ ዘግቧል። ማሮኮ አክለውም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የዩኤስ ኤአይዲ ሰራተኞችን ለመጥራት ፈቃደኛ የማይሆን ከሆነ፤ የአሜሪካ ጦር ሰራዊት እንደሚያስወጣቸው ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia