የሶሪያን መፈንቅለ መንግሥት ለማቀነባበር አምስት ዓመት እንደፈጀ የሀገሪቱ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ተናገሩ በጥር ወር ጊዜያዊ መሪ ሆነው የተሾሙት የሶሪያ የሽግግር ፕሬዝዳንት አህመድ ሻራ፤ የሃገሪቱን ዋና ከተማ ደማስቆ ለመቆጣጠር የተካሄደው ዘመቻ አምስት ዓመታትን እንደፈጀ ተናግረዋል ሲል የሶሪያ ቲቪ ዘግቧል። ሻራ በ11 ቀናት ውስጥ ፕሬዝዳንት ባሻር አሳድን ከስልጣን ለመገልበጥ የተካሄደው ዘመቻ ከሰሜን ምዕራብ ኢድሊብ ግዛት እንደተነሳ ተናግረዋል። በሐይማኖት ሳይሆን ህግን መሰረት ያደረጉ ተቋማትን መገንባት አስፈላጊ መሆኑንም አስገንዝበዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በሶሪያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለማካሄድ አራት ወይም አምስት ዓመታት እንደሚያስፈልግ የሶሪያ የሽግግር መንግስት መሪ አስታውቀዋል። "በሶሪያ ቀጣዩ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከአራት እስከ አምስት ዓመት ይወስዳል" ሲሉ ሻራ ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia