የኮንጎ አማፂያን በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል ከማክሰኞ ጀምሮ የተኩስ አቁም እንደጀመረ ይፋ አደረጉ ኤም23ን የሚያካትተው የኮንጎ ወንዝ ጥምረት፤ በምስራቅ ዲሞክራሲያዊ ኮንጎ የሰብዓዊ ተኩስ ማወጁን ኪቩ ኒውስ 24 ዘግቧል። ጥምረቱ ቡካቩን ወይም ሌሎች ከተሞችን የመያዝ እቅድ እንደሌለው ገልጾ፤ የሳድክ ኃይል ከአካባቢው እንዲወጣ ጠይቀዋል። ጎማ ባለፈው ሳምንት መያዙን ተከትሎ በከተማው የተመደበው የሳድክ ሰራዊት፤ የምግብ እና የውሃ እጥረት እንዳጋጠማቸው የተገለፀ ሲሆን፤ አማፂያኑ እርዳታ ለመስጠት ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ዘገባዎች አመላክተዋል። ኤም23 ጎማን የተቆጣጠረው በነሐሴ ወር የተደረገውን የተኩስ አቁም በመጣስ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሺሴኪዲ እና የሩዋንዳው አቻቸው ካጋሜ ውጥረቱን ለመቀነስ ቅዳሜ እለት ቁልፍ ስብሰባ ያካሂዳሉ።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia