ኢትዮጵያ በዓለም ቀዳሚ የምግብ ምርት ላኪ የመሆን አቅም እንዳላት የመንግሥታቱ ድርጅት ባለስልጣን ተናገሩ በትክክለኛ ኢንቨስትመንት እና ወደ አረንጓዴ፣ ዘላቂ እና ውጤታማ ኢኮኖሚ በሚደረግ ሽግግር፤ ኢትዮጵያ የራሷን የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ ባለፈ፤ በአፍሪካ እንዲሁም በዓለም ቀዳሚ የምግብ ሰብል አቅራቢ የመሆን ትልቅ አቅም አላት ሲሉ፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ ዶ/ር ራሚዝ አላክባሮቭ ተናግረዋል። ዶ/ር ራሚዝ አላክባሮቭ ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት ሁለት አስርት ዓመታት ከዓለም ቀዳሚ ኢኮኖሚዎች ተርታ ልትሰለፍ እንደምትችልም ጠቁመዋል ሲል የመንግሥት ሚዲያ ዘግቧል። ሀገሪቱ የአፍሪካን የእርዳታ ተቀባይነት ታሪክ በመቀየር እና የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን በማረጋጋጥ ረገድ ትልቅ ሚና እየተጫወተች እንደሆነም ነው የተናገሩት። ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ የጀመረችውን ትልቅ ሀገራዊ ተነሳሽነት ወደ ፊት ለማራመድ በምታደርገው ጥረት፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተልዕኮ ከሀገሪቱ ጀርባ መሆኑን ዶ/ር ራሚዝ አረጋግጠዋል ተብሏል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia